June 9, 2018 | Author: Adugna Toramo | Category: Documents


Comments



Description

ቀን 01/05/2010.ዓ/ም

ለአስተዳደር ዘርፍ መሰረታዊ ድርጅት

ሆሣዕና

ጉዳዩ፡- የባ/ቱ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ የሕዋስ ውይይት ሪፖርት ስለመለክ

በጉዳዩ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የመምሪያው ሕዋስ በቀን 01/05/2010.ዓ/ም የአባላት መደበኛ ውይይት አካሄዷል፡፡

ጥሬ ሀቅ

የመምሪያው የህዋስ አባላት ብዛት . ወ 18 .ሴ 18 .ድምር 36

በውይይቱ የተገኙ አባላት ወ. 8 .ሴ 4 .ድምር 12

በውይይቱ ያልተገኙ አባላት ወ 10 .ሴ 14 .ድምር 24 አባለቱ በውይይቱ ያልተገኙበት ምክንያት፡- በወቅታዊ
ጉዳይ፣በወሊድና በሌሎች ደረሽ ስራዎች ነው፡፡ በዚህም መሰረት የውይይቱ አጀንዳዎች፡-

1. የህዋስ የሁኔታ ግምገማን በተመለከተ፡-

2. ከኢህአደግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫን በተመለከተ

በውይይቱ ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች፡-

የአመለካከት ደረጃን በተመለከተ (በአውንታዊ ጎን)

- ከኢህአደግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በተሰጠው ድርጅታዊ መግለጫ መሰረት በአጠቃላይ

ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ በመገምገም ያለውን ችግሮችን በዝርዝር ያየበት ሂደት

ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን አባሉ በውይይት አረጋግጧል፡፡

- የተለዩ ችግሮች የህዝቡ ችግር መሆናቸውን አባላቱ በውይይት ወቅት ለመለየት

ችሏል፡፡

- ከአመራር እስከ አባላት ደረጃ የውስጣ ድርጅት ጥንካሬዎች ላይ ውስንነት

መኖረቸውን አባላቱ ለመየት ችሏል፡፡

- የሀገራችን ሁኔታ ከሠላምና ከልማት አኳያ ችግር ውስጥ እንደ ነበረ አባላቱ

ለመንሰት ችሏል፡፡

- የህዝብ ጥያቄን በአግባቡ ለይቶ አለመምረትና የህዝብ ትርታ አለማደመጥ




በግብዓት ደረጃ

- ከኢህአደግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተለዩ ችግሮችን ፈጥኖ ወደ ተግባር መቀየር እንደለበት አባላቱ በትኩረት
አንስቷል፡፡

- መንግስት በመልካም አስተዳደር ችግሮች (ከትልቁ አስከ ትንሹ) ላይ ተገቢ ርምጃ መውሰድ እንደለበት አባላቱ
በትኩረት አንስቷል፡፡

- አሁንም የህዝብ ጥያቄ የልተመለሱ በየቦታ ተጀምረው የልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች መኖረቸውን ጭምር አባላቱ
ለመሰየት ሞክረዋል፡፡

በክህሎት ደረጃ

- የተጀመረውን የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለመሰከት የአመራርና የአባሉ ውጤታማነት ዝቅተኛ መሆን

- በየቦታ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመየለት ፈጣን ምላሽ አለመስጠት

- የህብረተሰብን ፊላጎት ከተልዕኮ ጋር አቀነጅታው አለመምረት

- ለህዝብ ተጠቃሚነት ትኩረት አለመስጠት

ድጋፊና ክትትል በተመለከተ

- በአባሉና በአመራሩ ላይ ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር

- ለድጋፊና ክትትል ስራ የአባልና የአመራር ተነሰሽነት ዝቅተኛ መሆን

- መንግስት ለህብረተሰቡ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በቂ ግንዛቤ አለመፍጠር

በአውንታዊና በአሉታዊ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች

በአውንታዊ ጎን

- ድርጅታዊ መግለጫ ትክክለኛ መሆኑ

- ችግሮችን ቶሎ ለመለየት የተካሄደበት ሂደት ትክክለኛ መሆኑ

- የተለዩ ችግሮች የህዝብ ችግሮች መሆናቸውን

- አሁን ያለው የልማት፣ የሰላምና አንድነት ሂደት ቀጣይነት ያለ ቢሆን

በአሉታዊ

- አሁን የተነሱ/የተለዩ ችግሮች በጥልቅ ተሃድሶ ወቅት መለየት እንደነበረበት

- አሁንም እንደ ዞናችን የፀጥታ ስርዓት ችግር፣የፍትህ ስርዓት ችግርና የመሬት ወራረ ሁኔታ ቀጣይነት
መኖረቸው

- መንግስት ለተነሱ ችግሮች ፈጥኖ ምላሽ አለመስጣት

- መንግስት የህዝብ አመኔታ ለመግኘት በትኩረት አለመስረት

- በውጤታማነት ላይ አመራርና አባል ግንባር ቀደም ሚና አለመጫት

- በየቦታ ተጀምረው የልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች አሁንም የህዝብ ቅሬታ እየስነሰ መሆኑ

- የአመራርና የአባል ዝምታ በተግባር አፈፃፀም የሚንፃበረቅ መሆኑ

- የአገልግሎት አሰጣጥ በተለያዩ ተቋማት በጥገኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑ

- በአጠቃላይ በቀረቡ አጀንደዎች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ አባሉ ለውጤታማነት በቁርጠኝነት መታገል
እንደለበት፣የኢህአደግ ስራ አስፈፃሚ አባላት ከድርጅት ኃላፊነት እንደሚነሱ በአባላት በአመለካከት ደረጃ
ለተነሱ ጉደዮች ከመድረኩ ግልጽናትና ግንዛቤ ለሚፈልጉ ጉዳዮች ጭምር በቂ ምላሽ በመስጠት፣በቀጣይ አቅጣጫ
ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ ድምደሜ ላይ ተደርሷ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
















































ቁጥ----------------------

ቀን 03/04/2010.ዓ/ም



ለሀዲያ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ

ሆሳዕና



ጉዳዩ፡- የመኪና ትውስት ስለመጠየቅ

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለመንግስታዊ ስራ ጉዳይ የመ/ቤታችውን መኪና በትውስት እንዲፈቀድልን በትህትና
እንጠይቃለን!!

ከሰላምታ ጋር!!



ግልባጭ፡-

ለመምሪያ ኃላፊ

ሆሳዕና







ታህሳስ


2008.ዓ/ም

የሀዲያ ባህላዊ ሙዚቃ ጭፈራዎችና የሙዚቃ መሳሪያዎች በአጭሩ ሲቃኝ




ስነ- ቃሎች ከባህላዊ ትውፊትነት ባለፈ የአንድ ብሄረሰብ/ሕዝብ/ እምነትና ስሜት መገለጫዎች ናቸው፡፡
ብሔረሰብን/ሕዝብን/ የማስተማር፣ የመገሰጽ፣ መልካም ስነ-ምግባርንና በህሪን የማወደስ፣ መጥፎውን ደግሞ የማውገዝና
የማነቃቃት ሚና ስለላቸው የአገራችን ማህበረሰብ በተለይም አርሶ አደሮች በማህበራዊና ባህላዊ ሁነቶች ላይ በስፋት ስጠቀሙ
ይታያል፡፡

ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል እየተለለፉ ከመጡት ከበርካታ ስነ -ቃል ክፍሎች አንዱ የሆነው ባህላዊ ሙዚቃ
በአገራችን በሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ በደስታ፣ በሐዘን፣ በበዓለት እንዲሁም በገጠራማ የአገርቱ ክፍሎች በአዝመራ
ወቅት ስራው እንድቀላጠፍና ድካም እንደይዝ በሕብረት ይዜማል፡፡

ባህላዊ ሙዚቃ የዜማውና የግጥሙ ባለቤት ቢኖርም የሚያዜሙቸው ሕዝብ ነው፡፡ ሙዚቃዎቹ እንደ የብሔረሰቡ ማንነት፣
ታሪክ፣ ወግ፣ እሴትና የአኗኗር ስርዓት የራሳቸው የሆነ የአዘፋፈን፣ የአጨፋፈርና የውዝዋዜ ስልት አላቸው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ስለ ሀዲያ ባህላዊ ሙዚቃ መሳሪያዎች ጥቂት መረጃ ሰጥተን የተወሰኑ ባህላዊ ሙዚቃዎችን
እናስቃኛለን፡፡ የሀዲያ ብሔረሰብ ደስታውንም ሆነ ሐዘንን እንዲያደምቅለት የሚጠቀማቸው በርካታ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች
ሲኖሩት በዋናነትም ክራር፣ ዋሽንት፣ ከበሮ፣ ነጋሪት፣ ማስንቆና ጫቻ ይጠቀሳሉ፡፡ መሳሪያወቹም የትንፋሽና የምት ተብሎ
ለሁለት የሚከፈል ሲሆን አይደለም የሰውን የእንሰሳትን ጆሮ የማንቆርቆር አቅም ያላቸው ናቸው፡፡

ሀ.ክራር (ዲታ)፡- መሳሪያው ሀድዮች ሀዘንና ደስታን ለመግለጽ ከልማድ ባገኙት እውቀት ከፈጠሩአቸው ከምት
የሙዚቃ ኪነ- ጥበብ ስራዎች አንዱ ነው፡፡ ብሔረሰቡ ክራርን የሚጠቀመው ለሰርግና ለሌሎችም ማሕበራዊ ክዋኔዎች
ለማጀብያነት ነው፡፡

መሳሪያው መቼ እንደተፈጠረ የሚገልጽ መረጃ ለጊዜው ባይገኝም ብሔረሰቡ ከጥንትም ጀምሮ ክራርን በጠቶቹ እያነጋገረ
ሲዝናና እንደ ነበር የብሔረሰቡ ዕድሜ ጠገብ ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ መሳሪያው የሚሰራው በቆዳና በእንጨት ሲሆን የተለያዩ
ድምጾችን የሚሰጡ አምስት ክሮችም አሉበት፡፡

ለ. ዋሽንት (ገምበቢያ)፡- ዋሽንት (ገምባቢያ) የሚባለው የሀድያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ደግሞ ከቀርከሀ
የሚሰራ የትንፋሽ መሳሪያ ሲሆን ልዩ ልዩ ድምጾችን የሚሰጡ አምስት ቀዳዳዎች አሉበት፡፡ ብሔረሰቡ ዋሽንትን የሚጠቀመው
በብሔረሰቡ ዘንድ በደማቅ ሁኔታ የሚከበረው የመስቀል በአል እየደረሰ መሆኑን ለማብሰር ሲሆን የሚነፋውም ከቡሄ
(ከግረቾታ) መግስት ጀምሮ እስከ መስከረም አስራ አምስት (ፉልጥ ባለ) ድረስ ነው፡፡ የሙዚቃ መሳሪያውን የሚነፉት
በየትኛውም የእድሜ ክልል የሚገኙ ወንዶች ሆኖ በአብዛኛው ግን ወጣቶች ለበዓሉ የሚያስፈልጉትን የቅድሚያ ዝግጅት
ስራዎችን እየሰሩና ከብቶችን እየጠበቁ ነው፡፡







ሐ. ጫቻ፡- ጫቻ ሌላኛው በቀርከሃ የሚሰራ የትንፋሽ መሳሪያ ሲሆን ከዋሽንት የሚለየው በድምጽ ቅጥነትና ርዝመቱ
እስከ ሁለት ሜትር የሚረዝም በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የሙዚቃ መሳሪያ እንደሌሎቹ የሀዲያ ባህላዊ ሙዚቃ መሳሪያዎች ብቻውን
ፋይዳ ያለውን አገልግሎት መስጠት ስለማይችል ብሔረሰቡ ለሌሎች ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች ማጀቢያነት ነው የሚጠቀመው፡፡

የድምጽ ቅላጼ በጣም ቀጭንም ቢሆን የራሱ የሆነ ውበት አለው፡፡ መሳሪያው ረጅም ትንፋሽ ስለሚፈልግ ልምድ ካላቸው
ግለሰቦች ውጪ ማንም ተነስተው መንፋት የማይችል ሲሆን ብሔረሰቡ ይህንን መሳሪያ የሚጠቀመው ለለቅሶውና ለግርዛት ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በብሔረሰቡ ዘንድ ብዙም ተፈላጊ በለመሆኑ በቀላሉ መገኘት እንደመይቻል ነው አንዳንድ የብሔረሰቡ ተወላጆች
የሚነገሩት፡፡

መ. ከበሮ (ጠርቤ) ፡- ከበሮ የሚባለው በህላዊ የምት የሙዙቃ መሳሪያ የሚሰራው በሸክላና በቆዳ ሆኖ ማህበረሰቡ
በበአለትና በተለያየ ክዋኔዎች ይጠቀማል፡፡

ሠ. ማስንቆ (ማሲንቆኦ)፡- ማስንቆ የብሔረሰቡ ተወላጆች በደስታ፣ በበአላት፤ በልማት ስራዎችና በሌሎችም
ማህበራዊ ክንዋኔዎች ለመዝናኛነት የሚጠቀሙበት በህላዊ የሙዚያ መሳሪያ ነው፡፡ መሳሪያው በቆዳና በእንጨት ተሰርቶ
የሚፈለገውን ድምጽ አንዲሰጥም የፈረሰ ጭራ በቀጭኑ ተገምደው ይታሰራል፡፡ ማስንቆ ለብሔረሰቡ ጥንታዊ ሙዚቃ መሳሪያዎች
ከሆኑት ውስጥ አንዱ ከመሆንም ሌላ ልዩ ልዩ ድምጾችን ስለሚሰጥ በብሔረሰቡ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው፡፡ ማስንቆን
በአብዘኛው የሚጨወቱት የመጨወት ተስጥኦ ያላቸው ወንዶች ናቸው፡፡

ሸ. እምቢልት/ጡሩንባ/ ፡- እምቢልት ሌላኛው የሀዲያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆን የህብረተሰቡ ለለቅሶው፣
ለሰርግ፣ ለአደን፣ ለስብሰባና ለማህበራዊ ጉዳዩች ጥሪ (ለምሳሌ፡-ሞሰሶን ለማቆም፣ ታማምውን በቀሬዛ ወደ ጤና ተቋማት
ለመውሰድና ለሌሎችም ማህባራዊ ጉዳዮች) ይጠቀማል፡፡ እምብልት የሚሰራው በድኩላና በአጋዘን ቆዳ እንዲሁም በቀንድ
ነው፡፡ ይህንን የትንፋሽ መሳሪያ በየትኛውም የእድሜ ክልል ያለው ወንድ መንፈት የሚችል ሆኖ በአብዛኛው ግን ረጅም
ትንፋሽ ማቋቋም የሚችሉ ወንዶች ናቸው የሚነፉት፡፡

ቸ. ነጋሪት (ነጋሪታ)፡- ይህ የሀዲያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ ከምት ሙዚቃ መሳሪያዎች አንዱ ነው፡፡ መሳሪያው
የሚሰራው በእንጨትና በቆዳ ሲሆን ከከበሮ/ ከጠርቤ/ የሚለየው በትልቅነቱና አንዱ በጀረባው ሲሸከም ሌላው በሁለቱም እጅ
የተለየ ስሜት በሚሰጥ መልኩ የሚመታ በመሆኑ ነው፡የሚመተው አንዱ በኩል ብቻ መሆኑም ሌለኛው ልዩነት ነው፡፡

ብሔረሰቡ ይህንን መሳሪያ የሚጠቀመው በማህበረሰቡ ዘንድ በተለያየ ስራዎች ግንባር ቀደም የነበሩት ሽማግሌዎች
ሲሞቱ ነው፡፡ ነጋሪቱን ማንም ሰው ተነስተው መጫወት አይችልም፡፡ በብሔረሰቡ ዘንድ በነጋሪት ተጫዋችነት የሚታወቁ
ሕዝቦች ስላሉ ለቅሶው ስከሰት ለእነሱ ሲነጋራቸው ነጋሪቱን ይዘው በመምጣት ይጨፍራሉ፡፡

የሀዲያ ብሔረሰብ በእነዚህና ባልተገለጹ በሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች የታደለ በመሆኑ በመሳሪያዎች በመታገዝ
በሚቀርቡ ሙዚቃዎች አማካኝነት የብሔረሰቡን በህል፣ ታሪክ፣ ማንነትና ወግ የሚገልጹ ባህዊ እሴቶችን እያስቃኘ ይገኛል፡፡

ከነዚያም መካከል ጥቂቶችን እንደሚከለተው እናስቃኛለን፡፡

1. ደረቦ ኡለዕ ሶዱኮ

ድምጽዊያን ተቀባዮች

ደረቦ ኡለእ ሶዱኮ 2X
ደረቦ ኡለእ ሶዱኮ 2X

ንዮኦ መቴና ክሎኦ ንዮኦ መቴነ ኪሎኦ

እኩዮቼ/ጓደኞቼ/ ሌሊቱ ነገ 2X "
እኩዮቼ/ ጓደኞቼ/ ሌሊቱ ነገ 2X

እህታችን ልትሄድ ተነሳች
እህታችን ልትሄድ ተነሳች"



አኖዕ ሞኦ ጨውኮ ደረቦ ኡለእ
ሶዱኮ 2x

"አባቶች አይተው ዝም አሉ" ንዮኦ መቴነ ኪሎኦ

አሞዕ ሞኦ ጨውኮ " እኩዮቼ/ ጓደኞቼ/
ሌሊቱ ነገ 2x

"እናቶች አይተው ዝም አሉ" እህታችን ልትሄድ ተነሳች"



አለጊ መሴነ ዋሩኮ

"ባዳ ልወሰደት መጣ"




ይህ ጭፈራ የሀዲያ ብሔረሰብ በሶስቱም የሰርግ አይነቶችና (በአንጋቻ፣ በእልሞቻና በኪፋ) በግርዛት ከምጨፍራቸው
ጨፈራዎች አንዱ ሲሆን ልዩ የሚደረገው የሙሽሪት ቤተዘመዶችና ሚዜዎች ከሌሊቱ አሰር ሳዓት አካባቢ ከማኝታ ተነስተው የኮሶ
መጠጣት ፕሮግራም ከመጀመሩ አስቀድሞ በቡድን የሚጨፈርበት ጭፈራ መሆኑ ነው፡፡ ወንዶችና ሴቶች በኬሻ (በጅባ) ክብ
ሰርተው በማቀመጥ ከበሮ (ጠርቤ) እየመቱ ሙሽሪቷንና ወላጆቿን ሆድ የሚያብሱ ቃላትን እየተጠቀሙ የሚጨፈርበት ሙዚቃ ሲሆን
ሙዚቃው በዋናናት ኮሶ ለማጠጣት ለሚጨፈረው ጭፈራ መንደርደሪያ ሆኖ ነው የሚያገለግለው፡፡

ጭፈራው የሚጨፈረው ሰርገኞች እንደ ነገ ሊመጡ እንደዛሬ ከሌሊቱ አስር ሳዓት አከባቢ በመሆኑ በዕለቱ ሙሽሪት
ከቤተሰቦቼ ጋር ለማሳለፍ የመጨረሻ ሌሊቴ ነው እየለች ታለቅሳለች፡፡ በጥሩ ድምጻዊያን ሴቶች መሪነት እየተጨፈረ የቆየው
ይህ ሙዚቃ በኮሶ አዘጋጅ ቡድን ኮሶው መዘጋጀቱ ሲረጋገጥ ጭፈራው ለስጦታ ጊዜ ወደሚሆን ጭፈራ ይቀየራል፡፡ በሰርጉ ጊዜ
የሚጠቀሙት የሙዚቃ መሳሪያ ከበሮ(ጠርቤ) ሲሆን ተዳሚዎቹ የተገኘውን ባህላዊ ልብስ ብለብሱም ሙሽሪትና ሚዜዎቿ ግን
በከብትና በበግ ቆዳ የሚሰራውን" ኪታ ከነጡቡቆ" ነው የሚለበሱት፡፡




2. አጎኔ አጎኔ ንዮኦ ሱጦ አጎኔ

ድምጻዊያን
ተቀባዮች

አጎኔ አጎኔ ንዮኦ ሱጦ አጎኔ
አጎኔ አጎኔ ንዮኦ ሱጦ አጎኔ

"አትጠጠም አትጠጣም እህታችን ኮሶ"
"አትጠጣም አትጠጣም እህታችን ኮሶ"

አጎኔ አጎኔ አኖዕ መሀ ኡዋቴ
እያሉ ይደጋግማሉ፡፡

"አትጠጣም አትጠጣም አባቶች ምን ሰጥተዋል"

አጎኔ አጎኔ አቡዊ መሀ ኡዋቴ

"አትጠጣም አትጠጣም ወንድሞቿ ምን ሰጥተዋታል"

በዚህ መልክ ሁሉንም ቤተዘመዶቿን ስም እየጠሩ ይጨፍራሉ፡፡ጭፈራው ከኮሶ መጠጣት ፕሮግራም አስቀድሞ ቤተዘመዶቿና
ከወላጀቿን ተከትለው በሰርጉ ዕለት የሚሰጡትን ስጦታ በሚያስወቅበት ጊዜ የሚጨፈር ነው፡፡ በጭፈራው የሚሳተፈው በየትኛውም
ዕድሜ ክልል ያለው ቤተዘመድ ሲሆን በዕለቱም ከወላጅ አባቷ ጀምሮ ሁሉም ቤተዘመድ በአቅሙ ስጦታ ለመስጠት ቃል ይገባል፡፡
በዚህ ጭፈራ ጊዜ ታዳሚዎችም ሆኑ ሙሽሪትና ሚዜዎቿ በደራቦ ኡላዕ ሶድኮ ጭፈራ ወቅት የለበሱትን ባህላዊ አለባሳት
ነው የሚለብሱት፡፡ ልክ የስጦታ ፕሮግራም እንዳለቀ የሙሸሪት የወንድሟ ሚስት ወንድሟ ያለገባ /የሌላት/ ከሆነ ደግሞ
የአጎት ልጅ ሚስት የተዘጋጀውን ኮሶ ለሙሽሪትና ለሚዜዎቿ እንዲሁም ሙሽሪትን ከልብ እንደሚወዷት ለመግለጽ አብሯት ለሚጠጣ
ቤተ ዘመድ ሁሉ "በሁንቡሎ/እንጀፋ" (በሸክላ የሚሰራ አንገታ ቀጭን የቦርዴ፣ የሻሜታ፣ የወተት . . . . መጠጫ)
አድረገ ራሷ ቀድማ ከቀመሰች በኋላ ትሰጣቿዋለች፡፡በባህሉ ኮሶውን ቀድማ መጠጣት የሚጠበቅበት የመጀመሪያ ሚዜ በመሆኑ
መጠጣት ትጀምራለች፡፡ ከዚያ በኋላ ሙሽሪቷና ወዳጆቿ ይቀጥላሉ፡፡



3. አጌ አጌ ድምፃዊን ተቀባዮች

አጌ አጌ (ጠጪ ጠጪ) አን ቡቻ አጌ (እኔ አፈር
ልብላ)

ደጋግመው ይላሉ ደጋግመው ይላሉ

ይህ ጭፈራ ከሰርግ ጭፈራዎች አንዱ ሲሆን የሚጨፈረውም ሙሽሪትና ወዳጆቿ ኮሶ በመጠጣት ላይ እያሉ ነው፡፡
የጭፈራው ዓለማው ኮሶ የሚጠጡትን ማደፋፈር ነው፡፡በሙዚቃው የሚሰተፉት በአብዛኛው ወጣቶች ሆኖ ክህሎት ያላቸው ጎልማሶችም
መሰተፍ ይችለሉ፡፡ በዚህ ሙዚቃ ከበሮ ዋናው የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆን ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው ክብ በመስራ እያጨበጨቡ
የሚጨፈሩት ጭፈራ ነው፡፡

4. ሱጦ ሹርቡ ሹርቡ

ድምጻዊያን ተቀባዮች

ሱጦ (ኮሳ)

ደጋግመው ይላሉ ሹርቡ ሸርቡ (ከደሙ ጋር ተዋህዶ)

ደጋግመው ይላሉ

ይህ ጭፈራ ሙሽሪትም ሆነች ተገራዦች ኮሶ ከጠጡ በኋላ የጠጡት ኮሶ እንድሰራ ታዳሚዎቹ ሙሽሪቱን /ተገረዡን/ ተራ በተራ
እየተሸከሙ የሚጨፍሩት ሙዚቃ ነው፡፡

ሙሽሪትም ሆነች ተገራዦች ኮሶ ከመጠጣታቸው የተነሳ እቤቱ ያሉት ታዳሚዎች በሙሉ በዚህ ሙዚቃ በመጨፈር ደስታቸውን
ይገልፃሉ፡፡ በዚህ ጭፈራ ከበሮን ነው ለሙዚቃ መሳሪያነት የሚጠቀሙት፡፡

5. ደዕል ሀያትቾ

ድምፃሚያን ተቀባዮች

ደዕል ሀያትቾ ሀያትቾ 2X

ደራ ሶዶና ደረቦ ጋዲ ጡማ ዎሬ ዎሮኮ (ያመጣል)

(ጧት ማለዳ ጀግኖችን በድል መልሰቸው) ደጋግመው ይላሉ፡፡

ይህ ሙዚቃ የሚጨፈረው ከማለዳ አስራ ሁለት ሰዓት አከባቢ ሲሆን ጭፈራው በዋናናት የአገሪቱን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ
የዘመቱት ጀግኖች በድል አድራጊነት እንደመለሱ ፈጠርን የሚጠይቁበት ነው፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ሙሽሪት /ተገረዡ/ የጠጡት
ኮሶ እንድሰረ ከሚጨፈረው ከ"ሱጦ ሹርቡ ሹርቡ" ቀጥሎ የሚጨፈር ሙዚቃ ነው፡፡ በዚህ ጭፈራ ወንዶች ፀጉራቸውን አፍሮ
አበጥረው ዱላና መፈቅያ ይዘው የሚጨፍሩበት ሆኖ ሴቶች ደግሞ ባህላዊ ጌጣ-ጌጦችን በአንገታቸው፣ በእጆቻቸውና
በእግሮቻቸው አድርገው ከበሮን እየመቱ ይጨፍራሉ፡፡

ከተራ ቁጥር 1—5 ያሉት ሙዚቃዎች ከሌሎቹ የሰርግ ጭፈራዎች የሚለዩት ከሌሊቱ አስር ሰዓት ገደማ (ከአንተባ ሙና) ጀምሮ
እስከ ጧቱ አስራ ሁለት ሰዓት እንቅልፍ ትተው የሚጨፍሩት ጭፈራ በመሆኑ ነው፡፡

6. ሂቦንጎ

ይህ ሙዚቃ ከታዳሚዎች መሀከል ጥሩ መቁጠር የሚችሉ ድምፃዊያን ተራ በተራ የሚያሟግሱትን እያሟገሱ የሚያጥላሉትን
በአሽሙር እያጥላሉ የሚጨፍሩት ሙዚቃ ሆኖ ተቀባዮቹ ግን በቡድን ነው የሚቀባበሉት፡፡ ሙዚቃው የሕዝብ ከመሆኑም ባሻገር
ድምፃዊያኑ ግጥሙ ቤት ይምታ እንጂ ስለሚጠሩት ቦታ፣ ግለሰብ ወይም ጎሳ ተዋቂነት ብዙም አይጨነቁም፡፡

ብሔረሰቡ ሙዚቃውን በሰርግ፣ በሚክራ ወቅት( ከመስቀል በአል በኋላ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ወንዶችና ሴቶች አንድ ላይ
ሆኖ በስንደዶ ለቀማ፣ ከገበያ ሲመለሱ፣ በእንጨት ለቀማ . . . ወዘተ የሚጨፍር ጭፈራ ነው) በፋሲካ በገናና በሌሎችም
ህዝባዊ መድረኮችና ክዋኔዎች ይጨፈረል፡፡

ከዚህ ውስጥ የገና በአልን በአብነት ብንወስድ በበአሉ ዕለት ወንዶች የገና ጨዎታ ሁለት ጎራ ሆነው ሲጫወቱ ሴቶች
የጫዎታ ሜደውን ከበው ተጫዋቾችን እያሞገሱና በአሽሙር እየሰደቡ ጨዎተው እስክጠነቀቅ ድረስ ሂቦንጎን ይጨፈራሉ፡፡



ሂቦንጎ የከንፈር ወዳጅ ለመፍጠር አመቺ ጭፈራ በመሆኑ አብዛኞቹ የብሄረሰቡ ጨፈርዎች/ተወዘዋዦች/ጥልቅ የመሰሳም
ተግባር የሚፈጽሙበት ነው፡፡ በወቅቱ የከንፈር ወዳጅዋ ከከንፈሯ ደም እስከሚወጣ ድረስ የሚስማት ሆኖ የሳማት የከንፈር
ወዳጅ የወጣውን ደም መጠው ማዋጥ ይጠበቅበታል፡፡ ካልመጣጠ እንደማይወዳት ነው የምትገምተው፡፡ስለሆነም ድርጊቱን/መሰሙን/
በአፈጠኝ ከልፈፃመ ሁለተኛ እንድስማት አትፈቅድም፡፡ ይህ ተግባር ሲፈጸም የዝሙት ትንኮሳ መፈጸም በባህሉ በጣም
አስነዋሪ ድርጊት ስለሆነ አብረው አንድ ቦታ ተቀምጠው ከመሳሳም ያለፈ አይተላለፉም፡፡ ሆኖም በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ
ተላላፊ በሽታዎች ስጋት የተነሳ ጥልቅ መሳሳም (Deep Kissing ) ሙሉ በሙሉ ቀርቷል፡፡




7. ያሆዴ ያሆዴ

ድምፃዊያን ተቀባዮች

ያሆዴ ያሆዴ 2X ሆ ሆ ያ ሆይ 2X

(የመስቀል በዓል) ሆ ሆ ያ
ሆይ

ዶምንሴ ሀቃ ጉሎ ሆ ሆ ያ ሆይ …

(ከዱር እንጨት ጨራሽ)

ዳጅንሴ ዎኦ ጉሎ

(ከወንዝ ውሃ ጨራሽ)

በርንሴ ዋሳ ጉሎ

(ከጎርጓድ ቆጮ ጨራሽ)




ያሆዴ ያሆዴ የሀድያ ብሔረሰብ በአመት አንድ ጊዜ በደማቅ ሁኔታ በሚያከበረው በመስቀል በአል ከሚጨፍራቸው
ከበርካታ ጭፈራዎች አንዱ ነው፡፡ ጭፈራው በዞኑ በአብዛኛው ወረዳዎች መስከረም አሰራ አምስት (ፉልጥ በላ) ምሽቱን በሙሉ
የሚጨፈር ሲሆን ከሌሎች የብሔረሰቡ ጭፈራዎች የሚለየው ልጆች ወላጆችን የሚመረቁበት በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ሙዚቃ በየ
አካባቢው የሚገኙ ወንድ ወጣቶች ተሰብስበው ቤት ለቤት እየዞሩ የሚጨፍሩት ጭፈራ ሆኖ በገቡበት ቤት ሁሉ አተካና (ለበአሉ
ከሚዘጋጁ ምግቦች ግንባር ቀደም ባህላዊ ምግብ) እየበሉ የቤቱን አባወራዎችንና እማወራዎችን ይመርቃሉ፡፡

በምርቃቱ ወቅት የቤቱ እማወራዎችም/ አባወራዎችም/ ሆነ ልጆቻቸው የሚያመቸው፤ ልጅ ያልወለዱ /ልጅ የጠፈባቸው/
ሆኖ እስከ ቀጣዩ መስቀል በዓል ድረስ ከተፈወሱ /ከወለዱ ወይም ደግሞ ከተገኘ ከተለያየ ባህላዊ መጠጦች ጀምሮ እስከ
የፍየል/የበግ/ ሙኩት ለመስጠት ቃል ይገበሉ፡፡ ወጣቶቹ በዕለቱ ተራ በተራ እየተነሱ የሚኞታቸውን እንድየገኙ ይመርቃሉ፡፡
ምርቀቱም በአብዛኛው ግብ መቶ ይታያል፡፡ በገቡት ቃል መሰረትም የተሰሉትን ስለት አመቱ ሲደርስ ሳያሸረርፉ ስለሚሰጡ
ከአተካና በተጨማሪ ስለት በተገባበት ቤት ሁሉ ስጋ እየበሉና እየጠጡ ነው የሚያነጉት፡፡ ብሔረሰቡ በዚህ ጭፈራ ወቅት
የሚጠቀመው የሙዚቃ መሳሪያ እምቢልታ (ጡሩንባ) ሲሆን በዋናናት የሚገለገለው ዱለን ነው፡፡







8. ቦያ ሰሌሜ

ይህ ሙዚቃ በአብዛኛው ወንዶች ወገቦቻቸውን ተያይዘው ዝግዛግ እየሰሩ በበአላት፣ በሰርግና በልዩ ልዩ ክዋኔዎች
የሚጨፍሩት ጭፈራ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ሴቶችም ይሰታፋሉ፡፡ የቦያ ሴሌሜ ትርጉሙ "ቦያ" ብሔረሰቡ ለሴቶች የሚያወጣ
ስም ሲሆን "ሴሌሜ" ደግሞ እንከን የሌለባት ቆንጆ ሴት ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የጭፈራው ዋናው መልዕክት ማንም ሰው
በተሰማራበት የስራ ዘርፍ እንከን የሌለ ስራ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደለበት ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የሀድያ
ብሔረሰብ ሰርተው ለመለወጥ ደፋ ቀና የሚለውን የስራ ታታሪነቱን እጅ በእጅ በመያያዝ/እየተደጋገፈ/ የበለጠ ማሳደግ
እንደሚጠበቅበት ይገልጻል፡፡

በጭፈራው እለት ወደ ኋላ የሚቀሩት ተወዛዋዦች በአለንጋ የሚገረፉ ሲሆን መልዕክቱም ተያይዘን እንደግ እንጂ ወደኋላ
አትቅር ማለት ነው፡፡ በአለንጋ የሚመታ ተወዛዋዥ ምኑንም ያህል ቢጎዳ አያኮርፍም /አይጣላም/፡፡ ምክንያቱም ወደኋላ
ከቀረ እንደሚመታ አውቀው ነውና የሚገባው፡፡

9. አቡለን አሸሜ




ድምፃዊያን ተቀባዮች

አቡለን አሸሜ አሸሜ 2X ድምፃዊያኑ ያሉትን እንዳለ

(አርሶ አደሮች አሸም አይዞበርታ 2X ) እየደገሙ ይጨፍራሉ

አቡለኔ ስበር አጎኔ

(ርሃብን ለማጥፈት)

አኑለ በንጦነ አሸሜ

(መሬታችንን በሚገባ እንረስ)

ይህ ጭፈራ የብሔረሰቡ ወጣቶችና አዛውንቶች በዘር፣ በአረም፣ በኩትኳቶ፤ በአጨዳ፣ በውቂያ፣ በእንሰት ተክልና መፋቂያ፣
በድቅደቆና በሌሎችም የስራ ወቅቶች ከሚጨፍሩት ጭፈራዎች አንዱ ነው፡፡ ይህንን ጭፈራ ከሌሎቹ የስራ ወቅት ጭፈራዎች ልዩ
የሚያደርገው ስራ በሚሰራበት አካባቢ ከብት የጠበቁ/ያገዱ/እረኞች ስራ የሚሰሩትን አርሶ አደሮች ለማበረታታት የሚጨፍሩት
ሙዚቃ በመሆኑ ነው፡፡ ጭፈራው በአብዛኛው የሚጨፈረው በዘር ወቅት ሆኖ በሌሎችም የእርሻ ወቅቶች አልፎ አልፎ ይጨፈራል፡፡

ሙዚቃው ከአገሩ ርሃብ እንድጠፋ በርትተን እንስራ የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ በመሆኑ አርሶ አደሮች ከዕቅዳቸው በላይ
እንዲሰሩ የማነቃቃት ትልቅ አቅም አለው፡፡



















10. ሸምበላላዮኔ




ድምፃዊያን ተቀባዮች

ሸምበላላዮኔሄ ሸምበለላዮንኔ (ተጥለቅልቋል )

(ተጥለቅልቋል ) ይህንኑ ደጋግመው ይላሉ

ቡዶ ዕቆ ሞራዮንኔ

(ቀንድ ሰበር ሰንጋ ያለበት ነው)

ለሮ አለረንቾዮንኔ

(ከብት አርቢ ነው)

ሁርበታም ሴቾዮን

(ጎተራው ሙሉ ነው)

ብሔረሰቡ ይህንን ሙዚቃ የሚጠቀመው በወገና ስነ- ስርዓት (የከብቶች ቆጠራ ስነ- ስርዓት) ላይ ከከብቶቹ ቆጠራ ዋዜማ
አመሻሽ ላይ ሲሆን በአራስ ጭፈራና (በአድሳ) በሰርግ አልፎ አልፎ ይጨፈራል፡፡



ጭፈራው የሚያስተላልፈው መልዕክት የከብት፣ የእህልና የሚበሉ ምግቦች መምበሽበሻቸውን /መትረፍረዋቸውን/ ነው፡፡
በባህሉ መቶ ከብት መሙላቱን አረጋግጠው የሚያጸድቁት ከአሁኑ ቀደም መቶ ያስቆጠሩት ግለሰቦች ሲሆኑ ከነሱ በስተቀር በስራ
ስረዓቱ የተገኙት ዘመድ አዝማዶች ሁሉ በዚህ ሙዚቃ ይጨፈራሉ፡፡ አጽዳቂዎች የማይጨፍሩበት ምክንያት ከከብቶቹ ትንንሽ
ወይፈኖችን ሳይጨምር መቶ መሙላታቸውንና ፍየሎች በጎችና የጋማ ከብቶች መኖራቸውን እንዲሁም ቅቤ በባህሉ መሰረት በምን
ያህል እንስራ መኖሩን እስከረጋግጡ ድረስ ነው፡፡ የቆጠረ ስነ-ስረዓት የሚጀምረው ቀጣዩ ቀን ስነጋጋ ከሌሊቱ አስራ አንድ
ሰዓት አካባቢ ነውና፡፡ሙዚቃው ሞቅ ደመቅ እንዲል ከበሮ/ጠርቤ/የሚጠቀሙ ሆኖ "ኪታንና ለበሳን"(በቆዳ የሚሰሩ በህላዊ
አልባሳት)ጨምሮ የተለያየ በህላዊና ዘመናዊ ልብሶችን ለብሰው ነው የሚጨፍሩት፡፡

11. ሄቦ ሄቦ




ድምጻዊያን ተቀባዮች

ሄቦ ሄቦ

(ክበር ክበር) ሄቦ ሄቦ (ክበር ክበር)

አድሎዊ ቤቶ ሄቦ ደጋግመው
ይላሉ፡፡

(የነገስታት ልጅ ክበር)

ሆጉከንስ ሆራ ወሻ ወጮ ሄቦ

(ሽንፈትን የማታውቅ ክበር)

ኡል ሁንደም ገሴ ሄቦ

(አገርን ሁሉ አስተዳድር)

ኡሙር ቄራሌ ሄቦ

(እድሜህ ይርዘም)




የሀዲያ ብሔረሰብ እንደሌሎቹም ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ዳኝነት የሚሰጥበት ስነ-ስርዓት አለ፡፡ ማህበረሰቡ
ማስተዳደር ይችላል ብሎ የሚያምነውን ግለሰብ በእጅ ብልጫ ይመርጣል፡፡ ባህሉ በሚያዘው መሰረት የተመረጠው ባህላዊ
ዳኛም ዘመድ አዝማዶቹንና ሹመቱን ያጸደቁትን የጎሳ መሪዎችን ደግሰው ይጠራል፡፡እነዚያ ድግሱን ሊበሉ የሚመጡት
ተጋባዦች ከሚጨፍሩት ጭፈራዎች አንዱ ነው ሄቦ ሄቦ፡፡ ጭፈራው በአብዛኛው የአድሱን ዳኛ ብቃትንና ታታሪነቱን የሚገልጽ
ሆኖ ስለጎሳውና ብሔረሰቡ ልማታዊነትና ጀግንትም ይጠቀቅሳል፡፡ በዚህ ሙዚቃ የሚሳተፉት አዛውንቶች ሆኖ አዲስ
የተሾመውን የባህል ዳኛ ተራ በተራ እየተሸከሙ እያወደሱና እያሞገሱ ይጨፍራሉ፡፡

ተጋባዦቹ በተለይም የጎሳ መሪዎቹ አዲስ ለተሾመው ዳኛ አበጋዝ፣ አባገዳ፣ አስማቼ ዳናና ከመሳሰሉት ከሀዲያ ባህላዊ
የማዕረግ ስሞች እንዱን ስለሚሰጡ ጨፈሪዎቹም ይህንን የማዕረግ ስም እየጠሩ ነው የሚያሞግሱት፡፡በባህሉ ለአንድ ደኛ
የማዕረግ ስም ከተሰጠበት እለት ጀምሮ ማንም ስማቸውን መጥራት ስለማይችል፡፡በዚያን ዕለት አብዛኞቹ ጨፈሪዎች
የሚለብሱት "ቡሉኮ" ሆኖ አዲሱ ተሾሚ ግን ጀግንነቱን፣ ታታሪነቱንና ዕውቀቱን የሚገልጽ ባህላዊ የማዕረግ ልብስ ነው
የሚለብሰው፡፡

ከላይ በአጭሩ ለማብራራት የተሞከረው የሀዲያ ባህላዊ ጭፈራዎች አበይን በጭልፋ የመቅዳት ያክል ሆኖ ሁሉም ባህላዊ
ጭፈራዎች ባህሉንና ትውፊታቸውን ጠብቆ ለትውልድ እንደተላላፉ ከብሔረሰቡ አርቲስቶችና ከባህል ኪነት ቡድኖች ብዙ
የሚጠበቅ ይመስላል፡፡በሌላ ጎኑ ደግሞ በህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች በዘመናዊ መሳሪያዎች በመታከት መሳሪያዎቹ ለቀጣዩ
ትውልድ እንዳይተላለፉ ማነቆ እንዳይሆኑም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ቢሰጡ መልካም ነው እንላለን፡፡










ሆሳዕ





መውጫ

ተ.ቁ ርዕስ
ገጽ

1. መግቢያ /introduction/----------------------------------------------------
-----------1

2. የጥናቱ አላማ/objective/----------------------------------------------------
-----------1

3. የጥናቱ ዝርዝር ዓላማ/specific objective/ ------------------------------------
------1

4. የጥናቱ አስፈላጊነት /significance/--------------------------------------------
--------2

5. የጥናቱ ወሰን /delimitation/------------------------------------------------
----------2

6. የጥናቱ ውስንነት/limitation/-------------------------------------------------
---------2

7. የተዘጋጁት ጽሁፎች ዳሰሳ/reviw literature/ -------------------------------------
--- 3

8. የተገልጋይ አርካታ ምንነት-------------------------------------------------------
-------3

9. የጥናቱ ዘዴ/design of research/--------------------------------------------
---------4

10. የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ ---------------------------------------------------------
---------4

11. የመረጃ አሰባሰብ መሳሪያዎች/tools/-----------------------------------------------
-----4

12. የመረጃ አተናተን ዘዴ----------------------------------------------------------
--------- 4

13. የናሙና አወሳሰድ ዘዴ/sampling/------------------------------------------------
------4

14. Theoretical framework-------------------------------------------------
-------------5

15. Conceptual framework---------------------------------------------------
------------5

16. የአገከልግሎት አሰጣጥ ርካታ ደረጃ ማሳያ /index---------------------------------------
6

17. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ትንተና/secondary data/ -------------------------------------
---6

18. የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ትንተና/---------------------------------------------------
----- 6

19. የውጤት ግኝት/ results and findings/----------------------------------------
-------- 6

20. ሁለተኛ ደረጃ መረጃ ሰንጠረዥ-----------------------------------------------------
------6

21. የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ሰንጠረ----------------------------------------------------
------6

22. ማጠቀለያ------------------------------------------------------------------
---------------- 9

23. መፍትሄ ሃሳቦች--------------------------------------------------------------
------------ 10





ክፍል አንድ

1 .መግቢያ

የአምስት ዓመቱን እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ /GTP/በማሰካት ሀገራችንን ከድህነትና ከኋላ ቀርነት
በማላቀቅ መካከለኛ ኢኮኖሚ እድገት ደረጃ ካሉት ሀገሮች ተርታ ለማድረስ ተቋማት ቀልጣፋ /EFFICIENT/እና ውጤታማ/
EFFECTIVE/አገልግሎት ለተገልጋይ ህዝብ በመስጠት መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ /BPR/ አና /BSC/ እስታንደርድ
መሰረት የለውጥ ስራዎችን ሶስቱን አቋሞችን በመጠቀም የለወጥ ሰራዊት በማደራጀት ስር ነቀል የለውጥ ስራ አንቅስቃሴ
በመፍጠር መስራት ስፈልጋል ፡፡

የቋንቋና ስነ-ጥበብ እሴቶች የህዝብ ማንነት መገለጫ ብቻም ሳይሆን ለሀገራዊ ልማትም መሰረት ስለሆነ ባህለን
ከሌሎች ዘርፎች ጋር በማስተሳሰር ማልማት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ሆኗል፡፡በአሁኑ ግዜ የባህል ቱሪዝም በመላው ዓለም በጪስ
አልባነቱ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ይዞ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እደገት አንዲሁም በባህል ትውውቅ እና ልውውጥ ከፍተኛ
ሚና እየተጫወተ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም የዞኑን የቋንቋና ስነ-ጥበብ እሴቶች በማጥናት፤ በማልማት፤በመጠበቅ እና
በማስተዋወቅ የዞኑን መልካም ገጽታ ከማሳደግ አንጻር በቱባ ባህል ልማት ዙሪያ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ፡፡ በመሆኑም
ሁልጊዜ በመሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለወጥ /BPR/ ስታንደርድ መጠን ፤ጥራትና ጊዜ መሰረት ያደረገ አገልግሎት
ለተገልጋዮች መስጠት ልማትን ያፋጥናል ፡፡ ከዚህ አንጻር ሁል ጊዜ በየሩብ አመቱ የተገልጋዮችን የእርካታ እድገት ደረጃ
ለማወቅ መሰረታዊ የሆኑ የዳሰሳ ጥናት ማደረግ ይገባል ፡፡

ስለዚህ የቋንቋና ስነ-ጥበብ ጥናትና ልማት ስራ ሂደት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተገልጋዮች እርካታ ደረጃ ምን
ያህል እነደሆነ ተጨበጭ ውጤት ለማወቅ የዚህ ዓመቱን እርካታ ደረጃ የሚያሳይ ዳሰሳ ጥናት /survey/ግለጽ የሆኑ
መስፈርቶችን /criteria/ የያዘ መጠይቅ በማዘጋጅት የዘርፍን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ክፈተቶችን ለማሻሻል
ይህን የዳሰሳ ጥናት ከዞን እና ከወረዳ ተቋማት መረጃ በማሰባሰብ ጥናቱን አካሂዷል፡፡

2.የጥናቱ አላማ /General objective/

የተገልጋዮችን እረካታ አድገት ደረጃ በጥናት ለመለየት የስራ ሂደቱን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ማወቅና የታዩ
ክፍተቶችን ለማሻሻል ነው፡፡

3.ዝርዝር አላማ/Specific objective/

1. 1 .የዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ በስታንደርድ መሰረት መሆኑን ለማወቅ/to know service standards/

2. ተገልጋዮቻችን ምን ያህል በአገልግሎታችን እንደሚረኩ የአርካታ ደረጃ ማወቅ/to know satisfaction/

3. በጥናቱ የሚለዩ የአገልግሎት ችግሮችን ወይንም ክፍተቶችን በማሻሻል ተገልጋዮችን በከፍተኛ ሁኔታ ለማርካት /to



identify service limitation/



4 .የጥናቱ አስፈላጊነት/Significance of the study/

(1) .የስራ ሂደቱ አገልግሎት አሰጣጥ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን ለይቶ ለማወቅ ይጠቅማል ፡፡

(2) .የዚህ ጥናት ውጤት ለቀጣይ ስራዎች እነደ bench march ለመጠቀም ይረዳል ፡፡

(3) .የዘርፉን ተገልጋዮች ዕርካታ እድገት ደረጃ ባለድርሻ አካላት ለማሳወቅ ይጠቅማል ፡፡

(4) .ስራ ሂደቱ በአገ/ት አሰጣጥ በምን ደረጃ ላይ አንዳለ ለማወቅ መሳሪያ ይሆናል ፡፡

5 .የጥናቱ ወሰን /Delimitaion of the study/

የዚህ የዳሰሳ ጥናት ወሰን የሀዲያ ዞን ነው ፡፡በተለይም በዞኑ የሚገኙ የዘርፉ ተገልጋዮችና ባለድረሻ ተቋማት ናቸው
፡፡

6 .የጥናቱ ወሰንነት /Limitation of the study/

የቋንቋና ስነ-ጥበብ ጥናትና ልማት የስራ ሂደት ተገልጋዮች የዞኑ ሕዝብ ናቸው ፡፡ ይሁን እነጂ የዚህ ጥናት
አጥኚው ካለው የበጀትና የጊዜ እጥረት የተነሳ በዞኑ በገጠርና በከተማ የሚኖሩ ህብረተሰብ ክፍሎችን አንድ በአንድ
ተገናኝተወ ስለዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ አርካታ አስታያየቶችን ለመቀበል ስለማይቻል በዞኑ፤በወረዳዎችና በሆሳዕና ከተሞች
አስተዳደር ደረጃ የተወሰኑ ተገልጋይ ተቋማት በ simple random sampling>> ዘዴ በመጠቀም 20%ናሙና
በመውሰድ የዳሰሳ ጥናቱን ያካሄዳል ፡፡































ክፍል ሁለት

2.1 የተዛማጅ ጽሁፎች ዳሰሳ /LITETURE REVIEW/

እንደሚታወቀው አንድ ተቋም ውስጣዊና ውጫዊ ተገልጋዮች /customers or publics/ይኖረዋል
፡፡የተቋሙ ራዕይ ተልእኮና እሴቶችን ውጤታማነትን ከግቡ ለማድረስና ለማሳካት የተገላጋዮች አገልግሎት አሰጣጥ እርካታ
ወሳኝ ነው ፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ሴክተር የተገልጋይ እርካታን አስመልክቶ በተዘጋጀው የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ስልጠና
ሰነድ ላይ ሆልድዋይ (2001) ተገልጋይ ማለት ለአገልግሎት ሰጪ ተቋም ወሳኝና ቁልፍ አካል ነው(ገጽ 3) ከሆለድዋይ
ንግግር የምንረዳው አንድ ተቋም ወይንም መ/ቤት ተቋም ሆኖ ህልውናውን አሰጠብቆ አንዲኖር ከተፈለገ የውስጥ ፈጻሚዎችም
አነዲበረታቱና እንዲያድጉ ከተፈለገ የትገናዉም ተቋም የራሱ ውስጣዊና ውጫዊ ተገልጋዮችን በአገልግሎት አሰጣጥ ማርካትና
ማስደሰት አንዲሁም ሁል ጊዜ ጥራት ያለዉን አገልግሎት ቀጣይነት ባለው መልኩ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ለተገልጋዮች
መስጠት አማራጭ የሌለው ነገር መሆኑን ነው ፡፡ በመቀጠልም ጸሃፊው የተገልጋይ ፍላጎት ማሟላት ማለት ደግሞ በንጽጽር
የእርካታን ምላሽ ከፍ ማድረግ ነው ይላል ፡፡ የተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት /quality/ ያለወ መሆን ግድ
ነው ፡፡በተጨማሪም የተገልጋዮች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያላቸው እርካታ ለአንድ ተቋም በህይወት መቀጠል እጅጉን
አስፈላጊ እንደሆነ በርካታ ጽሁፎች ይስማሙበታል ፡፡

ስለዚህ አንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይንም የንግድ ተቋም ተቋማዊ ህይወት ቆይታ መሰረት የተገልጋዮች እርካታ
ስለሆነ ተቋሙ ሁልግዜ የዳሰሳ ጥናቶችን በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ አያካሄደ የሚታዩ ክፍተቶችን /ችግሮችን /እያሻሻለ
/አያስተካከለ /መሄድ አስፈላጊነቱ አማራጭ የሌለው ነው፡፡

2.2 የተገልጋይ እርካታ ምንነት

የተገልጋይ እርካታ /customer satisfaction/ስንል አንድ ህለውና ያለው ተቋም (ድረጅት)በሚያመርተው
ምርቶች በሚሰጣቸው አገልግሎቶች አሰጣጥ ወዘተ…. ተገልዳዮችየሚፈልጉትን ምርት (product)ወይም አገልግሎት
(service) በሚፈልጉት አይነት፤ ጥራት፤ መጠንና ጊዜ ስታንደርድ በማግኘት በቃልም ሆነ በጽሁፍ የሚገልጹት የእርካታ
ደረጃ ነው ፡፡ በሌላ አገላለጽ የተገልጋይ እርካታ ጥናት ማለትም ተቋሙ የሚያመርታቸው ምርቶችን (products)እና
የምንሰጣቸው አገልግሎቶችን (service) ካገኙ በኋላ ተገልጋዮቹ ወይም ስለ ምረቶች ወይም ሰለ አገልግሎቶች አሰጣጥ
እርካታ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ አስታየቶች አሰጣጥ እርካታ ደረጃ ለማወቅ የሚደረግ የዳሰሳ ጥናት ነው፡፡









ክፍል ሦስት

የጥናቱ ዘዴ/Methodology

3.1 .የጥናቱ ዘዴ/design of research/

በዚህ የተገልጋዮች የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ደረጃ ለማወቅ በሚደረገው የዳሰሳ ጥናት አጥኚው የሚጠየቀው
ገላጭ የዳሰሳ አጠናን

ዘዴ/descriptive survey design/ ነው፡፡

3.2. የመረጃ አሰባሰብ ዘዴ/method of data collection/

የዚህ የዳሰሳ ጥናት አጥኚው የጥናቱን የመረጃዎች ለመሰብሰብ የሚጠቀመው /primary data እና seconrey
data ዘዴዎች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ /primary data/መረጃዎችን ለማሰባሰብ መጠይቆችን /Questionnaires
በመዘጋጀት ከተመረጡ ተገልጋይ ተቋማት በ simple randomly sampling>>ዘዴ ይሰበሰባል ፡፡ሌላው የሁለተኛ
ደረጃ/seconrey data/መረጃዎችን ከስራ ሂደቱ ፈጻሚዎች /online/ፊት ለፊት አገልግሎት ያገኙ ተገልጋዮች
በመዝገብና በተዘጋጁ ፎርሞች አስታየቶችን ይሰጣሉ ፡፡በዚህ በ2008 በጀት ዓመት በስራ ሂደቱ ስር ከሚገኙ የቋንቋና
የስነ-ጥበብ ፈጻሚዎች 400 ሰዎች የመረጃ አገልግሎት የገኙ ሲሆን 398 ሰዎች (99.5%)መርካታቸውን በጽሁፍ ሲገልጹ
2 ተገልጋዮች ብቻ 0.5% በሙዚየም አገልግሎት አሰጣጥና አደረጃጀት ላይ አለመርካታቸውን ገልጸዋል ፡፡

3.3 .የመረጃ አሰባሰብ መሳሪያዎች/Tools of data collection/

አጥኚው ለዚህ ዳሰሳ ጥናት የሚሆን መረጃዎችን ከተገልጋዮች ለማሰባሰብ የተጠቀመው የመረጃ ማሰባሰቢያ የተጠቀመው
የመረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያ መጠይቆችን /structured questionnaires close ended
questionnaires) ነው

3.4 .የመረጃ አተናተን ዘዴ /Method of data analysis/

አጥኚው በመጀመሪያ የዳሰሳ ጥናቱን መረጃዎችን ከተገላጋዮች ወሰን መስፈርቶችን የያዘ መጠይቆችን
questionnaires አዘጋጅቶ ከዘርፉ አገ/ት ከሚያገኙ መ/ቤቶች ተገላጋዮች የሰበሰቡዋቸውን መረጃዎች ለመተንተን
የሚጠቀመው ገላጭ የመረጃ አተናተን ዘዴ /descriptive analysis ነው::

5. sampling procedure/የናሙና አወሳሰድ ዘዴ

የዚህ የጥናት አጥኚው የጠቀመው ገላጭ የናሙና አወሳሰድ ዘዴ /descriptive sampling
technique/ነው፡፡ምክኒያቱም አጥኚው simple rendom method በመጠቀም በሀዲያ ዞን ደረጃ ከሚገኙ
ተገልጋይ ተቋማት እኩል የመመረጥ እደል ሰጥተወ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ አሰባሰብ ስልት ተጠቅመው ጥናት አድረገውዋል
፡፡የዚህ የዳሰሳ ጥናት አጠቃላይ የናሙና መጠን (sampling size)ከ300 ተገልጋይ ህዝብ /population/ሲሆን
60 ተገልጋዮች(20%)ከተለያዩ 14 ተቋማት ናሙና sampling በመውሰድ አጥኚው ጥናት አድረጓል፡፡

Theoretical frame work of the study



Cusetomrs satisfaction is giving /offering servicees produtcts .etc for
customers by different organizations per needs of customers or according
to the inetersts of publics.



Independent variiable
Dependent variiable










Fig-1 showing the theoretical feramwork of study





Conceptual feramework

I/variiable
D/variiable
















Fig-2 showing conceptual feramwork of study





ክፍል አራት

መረጃ ትንተና /Data Analysis/

የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታ ደረጃ ማሳያ (Index of services)

ሁለተኛ ደረጃ መረጃ(Secondary data analysis)

በመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ከስራ ሂደቱ 20 ተገልጋዮች አገልግሎት አግኝቷል፡፡ በስራ ሂደቱ በቋንቋ፣ በስነ-
ጥበብ ዘርፎች ለተገልጋዮች የመረጃዎች አገልግሎት ይሰጣል ፡፡ አገልግሎቱን አግኝተው ሲያበቁ በBPR በተቀመጠው
ስታርዳንድ መሰረት ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ማግኘት አለማግኘቱን ወይም በአገልግሎቱ መርካታ አለመርካታቸውን በጽሁፍ
ያረጋግጣል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በቀረበው ሰንጠረዥ ይመልከቱ ፡፡

"ተገልጋይ "የረካ "ያልረካ "ደረጃ "
"የተገልጋይ ብዛት " 18 "2 "20 "
"(%) "91% "9% "100% "


Fig-3 ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ሰንጠረዥ

የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ትንተና primary data analysis

"ተ.ቁ "የአገልግሎት አይነት " የተገልጋይ " " "
" " "የአርካታ ደረጃ " " "
" " "1 "2 "3 "4 በጣም "የእርካታ ደረጃ " "
" " "ዝቅተኛ "አጥጋቢ "ከፍተኛ "ከፍተኛ " " "
"1 "የአገልግሎት አሰጣጥ ማእከላዊነት " " " " " " "
"2 "የአገልግሎት ተደራሽነት (accessibility)" " " " " " "
"3 "የአገልግሎት ብቃት (effectiveness) " " " " " " "
"4 "የአገልግሎት ጥራት (quality) " " " " " " "
"5 "የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍና (efficency)" " " " " " "
"6 "የፈጻሚዎች በለሙያዎች ቀጠሮ አክባሪነት " " " " " " "
" "(punctuality) " " " " " " "
"7 "የመረጃ ምላሽ ሰጪነት (responsiveness)" " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" "ድምር " " " " " " "


Fig-4 index of primary data services table





ውጤትና ግኝት /Results and findings/

ሀ/ ሁለተኛ ደረጃ መረጃ /Secondary data/

"ተ.ቁ "ተገልጋይ "ብዛት (መጠን) "(%) "ደረጃ "
"1 "የረካ "18 "91% " ከፍተኛ "
"2 "ያልረካ "2 "9% " ዝቅተኛ "
"3 "ድምር "20 "100% " "


Table 1፡- ሁለተኛ ደረጃ ሰንጠረዥ

ከለይ በሰንጠረዥ 1 እነደተመለከተው ከስራ ሂደቱ ፊት ለፊት (online)አገልገሎት ያገኙ ተገልጋዮች 200 ሲሆኑ 196
(98%) በአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ውጤት የረኩ መሆናቸውን ሲገልጹየተቀሩት 4(2%) ተገልጋዮች በባህል ቡድን
አደረጃጀትና አገ/ት አሰጣጥ ጥቂት ክፍተት መኖሩን አሳየተውን የማስተካከል እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ፡፡ በዚህ
በተገልጋዮች አስታየት ትንተና መሰረት ውጤቱ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል (የእርካታው ማለት ነው)፡፡

ለ/የመጀመሪያ ደረጃ/primary data/

"ተ.ቁ "መስፈርቶች (አገልግሎቶች" የተገልጋይ የአርካታ ደረጃ "ጠቅላለ "የርካታ ደረጃ"
" "ዓይነት) " "ድምር " "
" " "1 "2 (አጥጋቢ)"3 (ከፍተኛ)"4 በጣም " " "
" " "(ዝቅተኛ) " " "ከፍተኛ " " "
"1 "የአገልግሎት ማእከል "0 "0 "4 "56 " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " " "
" " " " " " " "ከፍተኛ ነው"
"2 "የአገልግሎት ተደራሽነት "5 "3 "30 "16 " " "
"3 "የአገልግሎት ብቃት "0 "6 "17 "30 " " "
"4 "የአገልግሎት ጥራት "0 "4 "24 "30 " " "
"5 "የአገልግሎት አሰጣጥ "6 "1 "21 "30 " " "
" "ቅልጥፍና " " " " " " "
"6 "የባለሙያዎች ቀጠሮ "1 "1 "30 "23 " " "
" "አከባበርነት " " " " " " "
"7 "ቶሎ ምላሽ ሰጪነትና "3 "5 "30 "20 " " "
" "የባህል ዕሴቶችን " " " " " " "
" "የማስታወዋቅ ስራ " " " " " " "
" " "40 "40 "100 "205 "392 " "
" "ድምር " " " " " " "
" "% " " " " "91 " "
" "index " " " " "3.92 " "


Table 2፡- የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ሰንጠረዥ



ከላይ በሰንጠረዥ -2 ውጤት እነደሚሳየው ከቋንቋና ስነ-ጥበብ ጥናትና ልማት ዘርፍ አገልግሎት ከሚያገኙት
ተቋማት(ተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላትን)በተወሰደው ናሙና (sample) መሰረት 15(0.15%) ተገልጋዮች ከዘርፉ
አገልግሎት አሰጣጥ ዝቅተኛ ደረጃ ነው ብለው ሲያስቀምጡ ዋና ምክኒያት አድርገው የሚያነሱት በባህል ሲምፖዚየም
አለመሳተፋቸውና የባህል ዘርፍ ሰዎችን ለይተው አለማወቃቸውን ነው፡፡ ከዚህ በኃላ በየዓመቱ በሚካሄደው የሃዲያ ባህል
ሲምፖዝየም በዓል ላይ ከሁሉም ተቋማት ሰዎች መሳተፍ የሚችሉበት ሁኔታ ለማመቻቸትና የተገልጋዮችን ፍላጎት
ለሟላት/ለማርካት ጥረት ይደረጋል፡፡

ሌላው ከተገልጋዮች 20(0.20%) የዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ አጥጋቢ ደረጃ እንሚገኝ አማረጭ ሁለትን በመምረጥ
ሲገልጹ 156(1.56%) ደግሞ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ርካታ ደረጃ ከፍተኛ ነው ብለው አመልክተዋል፡፡ይሁንና
አብዛኛቹ ተገልጋች የቋንቋና ስነ-ጥበብ የስራ ሂደት በሀዲያ፣ቋንቋ፣ኪነ ጥበብ(ኪነት)፣)፣ስነ-ጥበብ ወዘተ ዘርፎች
እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶች በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አማረጭ አራትን በመምረጥ አሳይቷል፡፡
በአጠቃላይ ከመጀመሪያ ደረጃ /Primary data/ ጥናት የተገኛው ውጤት ድምር cumulative result
392 ነው፡፡ ይህም በፐርሰንት ሲሰላ 392 ወደ 98% ከመቶ ወይም (392%) ይደርሳል ማለት ነው፡፡ ይህ
3.92(98/25)የርካታ ደረጃ ማሳያ( Index) የሚሳየው የተቋሙ(የዘርፉ) የተገልጋይ ርካታ ደረጃ በጣም ከፍተኛ
ደረጃ ላይ መውደቁን ነው፡፡ ስለዚህ በመዝገብ፣ በፎርማትና በመጠይቆች የተገኛ የደሰሳ ጥነት ውጤቶችን ጥቅልል አድርገን
ስናሰላ (99.04%) አማካይ ውጤት ይሳጠል፡፡

ይኸውም፡-

የሁለተኛ ደረጃ ውጤት= 91%)

የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት= 91%)

ድምር=182

አማካይ ውጤት = 182/2 = 91% ይሆናል፡፡

















የማጠቃለያ የመፍትሄ ሀሳቦች (conclusion and recommedatin)



ማጠቃለያ፡-

በዚህ የዳሰሳ ጥናት አጥኚው የቋንቋና ስነ-ጥበብ ጥናትና ልማት የስራ ሂደት አገልግሎት አሰጣጥ የደንበኞች እርካታ
ዕድገት ደረጃ ለማወቅ ከተገመተ ተቋማት አስተያበት በመውሰድ ጥናት አደርጓል፡፡

የጥናቱ ዋና አላማ በዘርፉ በሚሰጠው አገልግሎት አሰጣጥ የፈጻሚዎች የስራ ቅልጥፋና፣ ብቃት፣ የመረጃ ጥራት የቀጠሮ
አክባርነት ፣የስራ ውጤታማነት፣ የBPR አተገባበር ለተገልጋይ ምላሽ አሰጣትና የአገልግሎት ማዕከል ምቹነት ወዘተ
ደንበኞችን ምን ያህል እንደረካ የዕርካታ ደረጃና የሚታዩ ክፍተቶችን ለይቶ ለማወቅ ነው፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ አጥኚው ገላጭ የዳሰሳ ጥናት ዘዴ የተጠቀመ ሲሆን የመጀመሪ ደረጃ መረጃዎች አሰባሰብ "simple
random sampling" ዘዴ በመጠቀም በናሙናነት ከተወሰዱ /ከተመረጡ 60 ተገልጋዮች በመጠይቅ (structured
questionnaire) መረጃዎች ለማሰባሰብ ጥረት አድርጓል፡፡

በጥናቱ ውጤት መሰረት አብዛኞቹ ተገልጋዮች በተቋሙ ( በዘርፉ) አገልግሎት አሰጣት የእረካታ ደረጃ የተገለጹ ሲሆን
የተወሰኑት ቋማት ግን የመ/ቤታችንን አገልግሎት ዓይነት እንኳን ለይተው እንደማያውቁ ጭምር ገልፀዋል፡፡ስለዚህ የተለያዩ
ዘዴዎችን በመጠቀም በባህል ዘርፍ የሚሰማሩ ስራችዎን ወይም አገልግሎቶችን ማሳወቅ ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

በሌላ በኩል የዚህ ጥናት አጥኚው የቋንቋና ስነ-ጥበብ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከዞኑ ህዝብ ማንነት (identiy)
ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በጥናቱ ወቅት የተገኘው ውጤት ለሚሰሩ ስራዎች ወይም ለሚሰጡ አገልግሎቶች እንደ Benchmarch
ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአጠቃላይ የዘርፉ ተገልጋይ ርካታ ዕድገትና አገልግሎት አሰጣት ሁል ጊዜ የተያያዙ ነገሮች ስለሆኑ
ውጤታማ ፣ቀልጣፋና ጥራት ያለው ስራዎችን መስራት ከህዝቡ ማንነት ባሻገር ለኢኮኖሚ ልማትም ወሳኝ ነው፡፡



























የመፍቴሄ ሀሳቦች /recommendation/

ከጥናቱ የተገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ አጥኚው የሚከተሉትን አስያየት አስቀምጧል፡፡

የጥናቱ ውጤት መረጃ እነደሚጠቁመው በርካታ ተገልጋዮች ተቋማት በአገልግሎታችን ሊረኩ ካልቻሉባቸው ምክንያቶች በዋናነት
የአገልግሎት ጥራት፣ በሲምፖዚየም ህዝብን ያለማሳተፍና የኪነት አገልግሎትና ስነ ምግባር እና ቀጠሮ አለማክበር ጉድለቶችን
የጠቀሱ ስለሆነ ለቀታይ ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አብዛኞቹ ተቋማት የቋንቋና ስነ-ጥበብ ዘርፍ (ተቋም) የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አለማወቃቸውን
ይናገራሉ፡፡ በመሆኑ በዞናችን ለሚገኙ ተቋማት የባህል ስራዎችንን በተለያዩ ዘዴዎች ማሳወቅና አብዛኞቹ ወሳኝ የሆነው
ህብረተሰብ ክፍሎችን በሲምፖዚየምና በፌስትቫል በዓላት መሳተፍ የሚችሉበት ሁኔታ ሊመቻችላቸው ይገባል፡፡

እንደሚታወቀው አንድ ተቋም ሁለት ዓይነት ተገልጋዮች ( በውስጣዊና ውጫዊ) ይኖሩታል፡፡ የተቋሙ ህልውናም በነዚህ
ተገልጋዮች አገልግሎት ርካታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በመሆኑም ዘርፍ /ተቋሙ/የዞኑን ባህል በሰፊው ለሁሉም ህዝብ
በማስተዋወቅ የመ/ቤቱን ብሎም የዞኑን መልካም ገጽታ ማሳደግ ይጠበቅበታል፡፡

በዞናችን የባህል ዕድገት ከፍተኛ ቁንጮ ላይ ሊደርስ የሚችለው ባህልና የባህል መገለጫ ዋና መሳሪያ የሆነው የሀዲይሳ
ቋንቋ ከትምህርት ከቋንቋነት አልፎ የዞኑ የስራ ቋንቋ ሆኖ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት መቻልና በሚዲያዎች መጠቀም
ስንጀምር ብቻ ነው፡፡ መዝገበ-ቃላት (dictionary) ስነ-ቃሎች ወዘተ… ትኩረት ተሰጥቶባቸው ተሰብስበው፣
ተደራጅተውና ታትመው ለህዝባችን አገልግሎት እንዲሰጡ ተደራሽ መሆን ሲችል ብቻ ነው፡፡ በተጨማሪም የሀዲያ ታሪክ መጽሃፍት
ተጽፎና ታትሞ ለአገልግሎት ሲበቃ ነው፡፡

ኪነ ጥበብ የአንድ ህዝብ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች /ትውፊቶች/ ማንፀባረቂያ ነው፡፡ ሰለዚህ በዞኑ የቋንቋና ስነ-
ጥበብ ዘርፍ የተሰሩና እየተሰሩ ያሉ የስነ ጥበብ ስራዎች (ውጤቶች) ወይም የባህል ኢንዱስትሪዎች እንደ ፊልም፣ ድራማ
ዘፈን፣ጭውውቶች፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶች ወዘተ… ያሉ ስራዎች ዕውቅናና ድጋፍ አግኝተው ታትሞ ለህዝብ ዕይታ ለኢኮኖሚ
አገልልግሎት እንዲበቁ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡















የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት አፈፃፀም ምዘናና ደረጃ መግለጫ

የ1ለ5 አደረጃጀትና መመዘኛ

በ2009 ዓ.ም የ-------------ሩብ ዓመት---------------- (የአደረጃጀቱ ስም ይጥቅሳል) 1ለ5
አደረጃጀት የለውጥ አፈፃፀም ምዘና ዞን/ወረዳ /ከተማ ስም--------------የመ/ቤቱ ስም -----------------
---------------

"ተ/ቁ "መመዘኛ ነጥቦች "የክብደት "የአፈፃፀም ደረጃ "የምዘና ውጤት "
" " "ነጥብ "መግለጫ "ደረጃ "
" " "(%) " "×ክብደት/4 "
" " " "4 "3 "2 "1 " "
"1 "ወራዊ ሆነ ሳምንታዊ ዕቅድ ዝግጅት "12 " " " " " "
"2 "በመወያያ አጀንዳ መሰረት በቃለ-ጉባኤ የተደገፈ "6 " " " " " "
" "ውይይት " " " " " " "
"3 "የሪፖርት አቀራረብ "6 " " " " " "
"4 "መረጃ(ዕቅድ፤የአፈፃፀም ሪፖርት ፤አባላት በስታንዳር "8 " " " " " "
" "መሰረት አገልግሎት የሰጡበት መረጃ፤ ግብረ-መልሶች " " " " " " "
" "፤ቃለ-ጉባኤዎች የስልጠና ዶክመንቶች እና ሌሎችም) " " " " " " "
" "አያያዝና አደረጃጀት " " " " " " "
"5 "ደረጃ አሰጣጥ "5 " " " " " "
"6 "ለአባላት ግብረ መልስ አሰጣጥ "6 " " " " " "
"7 "የ1ለ5 ውይይት ቃለ-ጉባኤ መረጃዎችንና ግብረ-መለስን"7 " " " " " "
" "ለሰራተኞች ባህሪ ምዘና ለመጠቀም እየተደራጀ መሆኑ " " " " " " "
"8 "የክራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር እንዲሁም ላይ"25 " " " " " "
" "የሚደረግ ትግል " " " " " " "
"9 "ዕቅድ አፈፃፀም "25 " " " " " "
" ድምር "100 " " "


--

የለውጥ ቡድኑ መሪ ስም ----------------------------

ፊርማ ---------------------------------

ቀን -----------------------------------------











ቁጥር---------------------

ቀን-------------------
---

ለአቶ---------------------------

ባሉበት



ጉዳዩ፡- የሀዲያ ብሄር 14ኛ ዙር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ"መስቀላ" በዓል

የ----------------------------ኮሚቴ መሆኖዎን ስለማሳወቅ፤

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በዘንድሮ ዓመት የሀዲያ ብሄር ዘመን መለወጫ ያሆዴ መስቀላን በዓል ልዩ በሆነ
መልኩ እንዲከበር ተወስኗል፡፡

ስለሆነም እርሶ በዓሉ የተሰካና የታለመላትን ግብ እንዲመታ ዘንድ የ-----------------------------ኮሚቴ
ሆነው የተሰየሙ መሆኖዎን እየገለጽኩ የተጠለቦትን ኃላፊነት በታታሪነትና በብቃት እንዲወጡ አሳስባለሁ፡፡

ከሠላምታ ጋር!



ግልባጭ፡-

ለያሆዴ መስቀል አስተባበሪ ኮሚቴ

ለያሆዴ መስቀል ዋና አዘጋጅ ኮሚቴ

ለሀዲያ ዞን ባ/ቱ/መ/ኮ/ጉ/ መምሪያ

ሆሳዕና



















ቀን 05/08/09.ዓ/ም

ለሀዲያ ዞን አስተዳደር ዘርፍ መሰረታዊ ድርጅት

ሆሳዕና

ጉዳዩ፡- የሕዋስ ውይይት ሪፖርት ስለመላክ

በጉዳዩ እንደተጠቀሰው በአዲስ ራዕይ ቅጽ 5 ቁጥር 7 ጽሁፍ ላይ ህዋሱ ውይይት እንዲያደርግና ግንዛቤ እንድጨብጥ
በቀረበው መሰረት የውይይቱ ይዘት ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡

በተሳትፎ መገኘት ያለበት ወ. 19 ሴ. 11 ድ. 30

የተገኙ ወ. 8 ሴ. 8 ድ. 16

የመምሪያው አባላት በተገኙበት የአዲስ ራዕይ ቅጽ 5 ቁጥር 7 ጽሁፍ ዋና ዋና አጀንደዎች፡-

1. ከስር መሰረታቸው ይነቀሉ ያልናቸው ጠባብነትና ትምክህተኝነት አሁን የት ደረሱ?

2. ጅምሩ በጥልቀት የመታደስ ጉዞአችን በሚል ላይ ከመጽሔቱ አባለቱ በንባብ ባገኙት ግንዛቤ ላይ ካለው ነበራዊ
ሁኔታና የፅሁፉን ይዘት በተመለከተ በሰፊው ግንዛቤ ማስጨበጫ በመምሪው ኃላፊ የቀረበ ሲሆን፡-

በውይይቱ ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች

በከተማ ፅዳትና ውበት አሁንም ጉድለቶች መኖሩ

የሆሳዕና ከተማ የፋይነንስ አሰራር ከኪረይ ሰብሳቢነት ያልፀዳ መሆኑ

የዞኑ የንግድ ቁጥጥር ስርዓት ችግር ያለበበት መሆኑ

በከተማ በንግድ ስርዓት ላይ የቨት አመዘጋገብ ላይ ጎሳኝነት ያለ መሆኑ

በሆሳዕና በቤተል ቀበሌ በመንገድ ግንባታ በከሳ ክፍያ ላይ ኪራይ ሰብሰቢነት ያለው መሆኑ

የሆሣዕና ከተማ የመሬት አስተዳደር ልማት አሁንም ከፕለኑ ይልቅ ህገ-ወጥ አሰራር የቀደማ መሆን

በዞኑ የሰው ኃይል ቅጥር ላይ ጠባብነትና ጎሳኝነት ያለው መሆን

በዞኑ ፖሊስ ዝውውርም ቅጥር ሆነ ጠባብተኝነትን መሰረት ያደረገ መሆኑ በከተማ ፀጥታ ላይ ችግር
እየፈጠረ መሆኑ

በተሃድሶ ወቅት የተፈፃሙ ርምጃዎች ለህ/ሰቡ ግልጽ አለመሆንና የውሳኔ ሰጪነት ክፍተት መኖሩ

የከተማ የውሃ፣ማብራት መቆራራጥ በህዝቡ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተፅኖ እያደረሰ መሆኑ

የመልካም አስተዳደር ችግር ከፍትህ ስርዓትና ከሰው ኃይል ዝውውር ችግር መኖሩ

ድርጅቱ ለየትኛውም ችግር ፈጣን ምላሽ አለመስጠት

በአጠቃላይ በቀረበው አጀንደዎች ላይ ሰፊ ውይይት በመካሄድ ትምክህተኝነትና ጠባብነት ለሀገር ልማት
ማነቆ መሆኑን አባለቱ በቂ ግንዛቤ በመግኘት እንዲሁም በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጉዳዮች ከመድረክ
ምላሽ በመስጠት በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡




ቀን 05/07/09.ዓ/ም

ለአስተዳደር ዘርፍ መሰረታዊ ድርጅት

ሆሣዕና

ጉዳዩ፡- የባ/ቱ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ የሕዋስ ውይይት ሪፖርት ስለመላክ

በጉዳዩ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የመምሪያው ሕዋስ በቀን 01/07/09.ዓ/ም የአባለት መደበኛ ውይይት አካሄዷል፡፡
በዚህም መሰረት የውይይቱ አጀንዳዎች፡-

1.ከጥልቅ ተሃድሶ ውይይት ማግስት ምን ምን ለውጦች አሉ? እንደ ችግር የቀጠሉ ጉዳዮችስ ምን ምንድናቸው?

- ከመልካም አስተዳደር አንጻር

- ከአገልግሎት አስጣጥ አንጻር

- ኪራይ ሰብሳቢትን ከመታገል አንጻር

የመምሪያው የህዋስ አባለት ብዛት .ወ 19 .ሴ 11 .ድምር 30

በውይይቱ የተገኙ ወ 6 .ሴ 6 .ድምር 12

በውይይቱ ያልተገኙ ወ 13 .ሴ 5 .ድምር 18

አባለቱ በውይይቱ ያልተገኙበት ምክንያት፡- በወቅታዊ ጉዳይ እና በሌሎች ስምርት ስራ ምክንያት ነው፡፡



በውይይቱ ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች በተቋሙ ከጥልቅ ተሃድሶ ማግስት ጀምሮ፡-

- ውጤታማ የአገልግሎት አሳጠጥ የተዘረጋ መሆኑ፤

- የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት የሥራ ሰዓት በአግበቡ ከመጠቀም አኳያ መሻሻሎች መኖሩ

- የግብዓት አጠቃቀም ክፍተቶች ላይ መሻሻል መኖሩ

- የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በተደራጃ ሁኔታ መምራት እንደለበት

- የተቋሙ ውስጣዊ አስተዳደር በክህሎት እየተሰራ መሆኑ

- ባለሙያዎች ተግባራትና ክህሎትን መሰረት አድርጎ እየሰሩ መሆናቸው

- የሚዲያ ዘርፍ ተልዕኮን ከመወጣት አኳያ መሻሻሎች መኖሩ

- በተቋሙ የነበረው የዕቅድ ዝግጅት ክፍተት የተቀረፈ መሆኑ….ወዘተ፡፡

እንደ ዋና ዋና ችግር የተነሱ ጉዳዮች

- በዞኑ የመንግስት ሰርተኞች የደመወዝ መሻሻያ ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ዕቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ



- የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በተደራጃ ሁኔታ አለመማራት

- የህዋስ ውይይትና የልሳነት አጠቃቀም አለመጠናከር

- የልሳናት አጠቃቀምና የድርጅት መዋጮ አሰባሰብ ላይ የደረሳኝ አሰጠጥ ክፍት መሻሻል አለበት የሚሉት ናቸው፡፡



በአጠቃላይ በዕለቱ ውይይት ከአባሉ ለተነሱ ጉደዮች ከመድረኩ ግልጽናትና ግንዛቤ ለሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ በቂ ምላሽ
በመስጠትና በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ ድምደሜ ላይ ተደርሷ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡



ቀን 15/07/09.ዓ/ም

ለአስተዳደር ዘርፍ መሰረታዊ ድርጅት

ሆሣዕና

ጉዳዩ፡- የባ/ቱ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ የሕዋስ ውይይት ሪፖርት ስለመላክ

በጉዳዩ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የመምሪያው ሕዋስ በቀን 15/07/09.ዓ/ም የአባለት መደበኛ ውይይት አካሄዷል፡፡
በዚህም መሰረት የውይይቱ አጀንዳዎች፡-

1. ከጥልቅ ተሃድሶ መድረክ ወዲህ ያለው መሻሻሎች በተለያዩ ዘርፎች ምን ይመስለሉ?

- ከአገልግሎት አስጣጥ አንጻር እና ኪራይ ሰብሳቢትን ከመታገል አንጻር

የመምሪያው የህዋስ አባለት ብዛት .ወ 19 .ሴ 11 .ድምር 30

በውይይቱ የተገኙ .ወ 4 .ሴ 5 .ድምር 9

በውይይቱ ያልተገኙ .ወ 15 .ሴ 6 .ድምር 21

አባለቱ በውይይቱ ያልተገኙበት ምክንያት፡- በወቅታዊ ጉዳይ እና በሌሎች ስምርት ስራ ምክንያት ነው፡፡



በውይይቱ ወቅት የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮች

ውጤታማ የአገልግሎት አሳጠጥ በመዘርጋት ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት እያተሰጣ መሆኑ፣

የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት የሥራ ሰዓት በአግበቡ ከመጠቀም አኳያ መሻሻሎች መኖሩ፣

የተቋሙ ውስጣዊ አስተዳደር በክህሎት እየተሰራ መሆኑ፣

ባለሙያዎች ተግባራትና ክህሎትን መሰረት አድርጎ እየሰሩ መሆናቸው፣

የተቋሙ ባለሙያዎች በቅንጅት መስረት እንደለባቸው፣



እንደ ክፍተት የተነሱ ጉዳዮች

በህዋስ ውይይት ላይ ሁሉም አባላት አለመገኘት

ውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጉደዮች ከመድረኩ ምላሽ በመስጠትና በቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት በማድረግ የጋራ ድምደሜ ላይ
ተደርሷ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡











በሀድያ ዞን ደኢህዴን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአስተዳደር ዘርፍ መሰረታዊ ድርጅት


የባ/ቱ/የመ/ኮ/ጉ/መመሪያ የህዋስ አባላት የ2010 በጀት ዓመት የአባል የግል ዕቅድ


የአባሉ ሙሉ ስም--------------------------------------


በድርጅቱ ያለው ኃላፊነት--------------------------------


በመንግስት ያለው ኃላፊነት-------------------------------


የስራ መደቡ መጠሪያ------------------------------------


የሚሠራበት የሥራ ሂደት--------------------------------


የዕቅድ ዓላማ


በድርጅትና በሴክተሩ የታቀዱ የልማት፣ የዲሞክራስና የመልካም አስተዳደር ግቦችን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሳካ ማድረግ፡፡


የዕቅዱ ግብ


በፖሊቲካና ርዕዮተ ዓላማዊ ዕውቀትን ማዳበርና የነቃ ተሳትፎ ማድረግ፡፡


በድርጅትና በመንግስት የታቀዱ ተግባራትን በግንባር ቀደምነት መፈፃም፡፡


ራስን ከኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ አድርጎ ሌሎችን በመታገል ልማታዊነትን ማረጋ






























በ2010 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት

ተ.ቁ "

ዝርዝር ተግባራት "

መለኪያ "መጠን "1ኛ ሩብ ዓመት "2ኛ ሩብ ዓመት "3ኛ ሩብ ዓመት "4ኛ ሩብ ዓመት "ምርመራ " " " " " "ሐ "ነ
"መ "ጥ "ህ "ታ "ጥ "የ "መ "ሚ "ግ "ሰ " " "1 "ወርሃዊ መዋጮ መክፈል "ብር " " " " " " " " "
" " " " " " "2 "የአዲስ ራዕይ መፅሄትና ጋዜጣ ደንበኛ መሆን "ብር " " " " " " " " " " " " " "
" "3 "አዳዲስ አባላትን ማፍራት "በቁጥር " " " " " " " " " " " " " " " "4 "በመደበኛ ህዋስ
ውይይት ግምገማዎች ላይ መገኘትና በንቃት መሳተፍ "በቁጥር " " " " " " " " " " " " " " " "5
"በመሰረታዊ ኮንፍራስ ላይ መገኘትና በንቃት መሳተፍ "በቁጥር " " " " " " " " " " " " " " " "6
"በድርጅቱ ህገ-ደንብ ላይ ከሌሎቹ አሰባላት ጋር ውይይት ማድረግና የአመላካከት ቀረፃ ስራ መስራት "በቁጥር " " " "
" " " " " " " " " " " "7 "ኪራይ ሰብሳቢት መታገል በተላይም የመንግሰት የስራ ሰዓትና ንብረት አጠቃቀም
ማሻሻል "በ% " " " " " " " " " " " " " " " "8 "በተቋሙ ውስጥ የሚጣዩ ፀረ-ዲሞክራሲያዊ
እንቅስቃሴዎችነ መታገል በተላይም ባለጉዳይ ማጉላላት፣ማመናጨቅና፣ፈፀንና ቀልጠፋ አግልግሎት መስጠት ብልሹ አሰራሮች ላይ
ትግል በማድረግ ማስተካከል "በ% " " " " " " " " " " " " " " " "9 "ዕቅዱን በስታንዳርዱ ቆጥሮ
ማከናዎን "በ% " " " " " " " " " " " " " " " "10 "የድርጅትና የመንግስት የተግባር ዕቅድ እንዲሁም
የለውጥ ስራዎቸን ግባር ቀደም በመሆን መፈጸም "በ% " " " " " " " " " " " " " "

" "11 "በድርጅትና በመንግስት የሚሰጡ ተጨማሪ ተልዕኮዎችን መፈፀም "በየ ሩብ ዓ " " " " " " " " " " "
" " " " "


ዕቅዱን ያዘጋጀው አባል ስምና ፊርማ ------------------------
ዕቅዱን ያፀደቀው የህዋስ አመራር ስምና-----------------------


ፊርማ---------------------ቀን---------------------------------
ፊርማ---------------------ቀን---------------------------------


























ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት
ቀን 25/07/09 ዓ/ም


ሀዋሳ፣


በመንግስት በተመቻቸው የስራ ዕድል በማህበር ተደራጅተን ተጠቃሚ መሆን ብንችልም ያመረተነውን ምርት ለገበያ አቅርበን
ተጠቃሚብ የመሆን ዕድል ባለመፈጠሩ የመበተን ስጋት አድሮብናል ሲሉ በሆሳዕና ከተማ መቴዮማ ብረታ ብረት ማንፋክቸርንግ
አክስዮን ማህበር አባላት ገለፁ፡፡


የሆሳዕና ከተማ ንግድ ኢንዱስትሪ ዋና ፅ/ቤት በበኩሉ ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት
በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡


የማህበሩ አባልና ዋና ሥራአስኪያጅ ወጣት ሊሬ ዲላሞ እንደገለጸው በ2006 ዓ/ም በ101 አባላት ከደቡብ ከፒታል ሊዝ
በተገኘው 48 ሚሊዮን ብር የተለያዩ መለዋወጫዎችን ለማምረት ዓላማ ሰንቆ ማህበሩ መቋቋሙን ገልፀው በአሁኑ ወቅት
በተለያዩ ምክንያቶች አባላት በመልቀቃቸው 66 አባላት ብቻ መቅረታቸውን ተናግረው፣


የማህበሩ አባላት የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎችን ብናመርትም ተገቢ የሆነ የገበያ
ትስስር ባለመፈጠሩና በቂ የሆነ የመንግስት ድጋፍና ክትትል ባለመደረጉ ኑሯቸውን መምራት የምያስችል ገቢ ባለመግኛታቸው
በአሁኑ ወቅት የመበተን ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል፡፡


እንዲሁም ወጣት መለሰ ለማ እና አስር አለቃ ገዛህኝ ኢያሱ በየበኩላቸው በኢንዲስትሪ የምትመራ ሀገር በመገንባት ከውጭ
በከፍተኛ ምንዛሪ ዋጋ ይገባ የነበሩ መለዋወጫዎችን በማስቀረት ሀገረ ውስጥ ከማምረት ባለፈም ወደ ውጭ መላክ የሚያስችሉ
ሥራዎችን እየሰሩ ቢሆንም ማህበሩ በአሁኑ ወቅት የሚጠበቅበትን ያህል መሥራት እንደልቻለ ተናግረው መንግስት ድጋፍና
ክትትል እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡


የሆሳዕና ከተማ ም/ካንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ ዋና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አየለ ገዴ በበኩላቸው መንግስት ለወጣቶች
የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሰፊ ዕቅድ ተይዞ መንቀሳቀስ መጀመሩን ገልፀው በአሁኑ ሠዓት በርካታ ወጣቶችም ተጠቃሚ መሆናቸውን
ጠቁመው፣


ለአብነትም መቴዮማ ብረታ ብረት ማንፋክቸርግ አክስዮን ማህበር አንዱ ሲሆን ማህበሩ በአንዳንድ ምክንያቶች ችግር ውስጥ
እንዳለ በመገምገም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቅረፍ በአመራር ቦርድ ደረጃ ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል ሲል የሀድያ
ዞን ባ/ቱ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ዘግቧል፡፡




በሀድያ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ስራ ሂደት በወረዳ የሚገኙ ስራ ሂደቶችን ለመደገፍ የተዘጋጀ
ቼክ ሊስት 2010 የወረዳው ስም ------------------- ----------------------------
ድጋፍና ክትትል የተደረገበት ቀን-----------------

የቼክ ሊስቱ አላማ ፡- የስራ ሂደቱ ከተቋቋመበት አላማ አኳያ የሚተገበሩ ተግባራት በሁሉም ወረዳዎችና
ከተማ አስተዳደር ውጤት ሊያስገኝ በሚችል ደረጃ ማከናወን እንዲችሉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ነው
፡፡

ድጋፍና ክትትሉ የሚያተኩርባቸው ነጥቦች

የለውጥ ስራዎችን በተመለከተ

2.1 የ15 ውይይት በየሳምንቱ አጀንዳ በመቅረፅ ውይይት ስለመደረጉ

2.2 ውይይቱን በቃለ ጉባዔ በመመዝገብ እያንዳንዱ ፈፃሚ ወራዊ ምዘና ስለመካሄዳቸው

2.3 የለውጥ ቡድን የ1ለ5 ቡድን አካላዊ ምዘና በየሩብ ዓመቱ በማካሄድ ግንባር ቀደሞችን የመለየት
ስርዓት ስለመኖሩ

2.4 የ1ኛው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግባራ አፈፃፀም ተገምግሞ የተደረሰበት መነሻ በማድረግ
የ2ኛው ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የሥራ ሂደቱ የ2010 መሪ ዕቅድ ስለመዘጋጀቱ /ስለመኖሩ

--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
-------------------------------

2.5 ተግባራት በስታንደርድ እየተመዘገበ እየተሰራ ከሆነ በመገለጫ ------------------------------
----------------------------------- -------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
-------------

2.6 ሳምንታዊ የተግባር ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርት ስለመኖሩ (ቢያንስ የ4 ተከታታይ ሳምንት ይታይ
)

-------------------------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------------------------
---- ---------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------- ---------------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------------------------

2.7 ከአመታዊ ዕቅዱ የግል ዕቅድና መርሃ -ግብሩ ተዘጋጅተው ፈፃሚና አስፈፃሚ ተፈራርሞ ወደ
ትግበራ የተገባ መሆኑ ፡-

--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------



2.8 ከዞን የወረዳውን የግብ ስምምነት ዕቅድ ከፈፃሚ ጋር ተፈራርሞ ወደ ትግበራ መገባቱ

--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------------------
----

2.9 የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ሪፖርት በጽ/ቤት ማኔጅመንት ተገምግሞ ለዞንና
ለሚመለከታቸው አካላት ወቅትን ጠብቆ ስለመላኩ ፡- ---------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
------------------------

2.10 በመንግስት ኮሙኒኬሽን ስራ ሂደት በማኑዋሉ መሰረት ተገቢው ባለሙያዎች ስለመሟላታቸው ---------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
-------------------------------------------፡-





2. 11. ተግባርን በሙሉ አቅም ማከናወን አንዲቻል አስፈላጊ ቁሳቁሶች ተሟልተው እያገለገሉ ስለመሆናቸው ፡-

ቪዲዮ ካሜራ (የሚሰራ) ---------------------------------------------------------
---------------------------------------------

አይሲ ሪከርደር (የሚሰራ ) ------------------------------------------------------
---------------------------------------------

ፎቶ ካሜራ --------------------------------------------------
-----------------------------------------------------

ስታንድ ---------------------------------------------------------
-------------------------------------------------

ፋክስ ---------------------------------------------------------
---------------------------------------------------

ኮምፒዩተርና ፕሪንረተር ----------------------------------------------------
------------------------------------------

2.12 በጀት አመቱ እስካሁን ድረስ በሶስቱም የሚዲያ ዘርፎች

በሕትመት - የህዝብ አስተያየት ፣ብሮሸር ------------------------------------------
---------------------------------------

በኤልክትሮኒክስ ዜና --------------------------------------------
--------------------------------------------

በገጽ ለገጽ የተሰሩ ስራዎች ስለመኖራቸው ናሙና በማሳየት ----------------------------
--------------------------------

2.13 የደቡብ ንጋት ጋዜጣ በየጊዜው ያለመንጠባጠብ ከዞን ማዕካል እየተወሰደ ለሚመለከተው አካል
እየተሰራጨ ስለመሆኑ --------------------------------------------------------------
--------------------------------------------------------------

2.14 ለወረዳው /ከተማ አስተዳደር በዙር የሚወሰደው የጋዜጣ ኮፒ ብዛት ስንት ነው ---------
---------------------------

2.15 የዞኑ ስራ ሂደት ከሚያዘጋጃቸው የህትመት ውጤቶች ( ካለንደር ፣ መጽሔት ) ፖስተር
ስለመድረሳቸው -------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
--------------

2.16 የተጠቀሱት የህትመት ውጤቶች ደርሰው ከሆነ ስንት ኮፒ እንደደረሱ እና በአግባቡ በወረዳው /ከተማ
አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ስለመታደላቸው -----------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
-------------------------

2.17 የወረዳው ጽ/ቤት ከዞኑ ማዕከል ጋር ያለ ግንኙነት ምን ይመስላል -----------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
---------------------- ግንኙነቱ ካለ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ከማሳወቅና በጋራ መፍትሔ
ከመፈለግ አንጻር የተተገበሩ እንቅስቃሴዎች ቢጠቀሱ --------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------------------

2.18 በወረዳው ካሉ ሴክተር ጽ/ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ጋር ተናቦ ከመስራት አኳያ ያለው እንቅስቃሴ ምን
ይመስላል ----------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------

2.19 የስራ ሂደቱ የስራ ማኑዋል ( በወረቀት እና በሶፍት ኮፒ ) ስለመኖሩ የስራ ሂደቱ የመረጃ
አያያዝ ሂደት እና የተለያዩ የስራ ማኑዋል ስለመኖሩ -------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------

2.20 የስራ ሂደቱ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተግባራት ስለመኖሩ --------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------

2.21 ያጋጠሙ ችግሮች -------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
----------------------------------------------------------------------------
------------------------

ድጋፍ ያደረገው
ባለሙያ ስም -----------------------------------------------

ቀን ---------------
-----------------------------






-----------------------
Services products

standard



Customers satisfaction needs



Services standards

.service location

.Effciency

. Effciency service

.Quality of service

.Availability (timeusing)





Customers needs

.satisfaction
Copyright © 2024 DOKUMEN.SITE Inc.